በኤች አይቪ ዙሪያ ያሉ መሰረታዊ መረጃዎች

ኤች አይቪ እና ኤድስ እንዴት ይከሰታሉ?

 

ኤች አይቪ በቫይረስ የሚፈጠር ሲሆን ኤድስ ደግሞ ከኤች አይቪ ኢንፌክሽን ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችል በሽታ ነወ።

ኤች አይቪ የሰዉነትን ከበሽታ የመከላከል አቅም ያዳክማል ፤ ሰውነታችን አንዳንድ በሽታዎችን መከላከል እነዳይችልም ያደርገዋል።

 • ኤች አይቪ በደም ውስጥ ኖሮ እንደ ሳምባ ምች ያለ ከባድ በሽታ ሲከስት ወደ ኤድስ ተሸጋገረ ይባላል
 • ለኤቸ አይቪ ኢንፌክሽን የሚደረግ የሕክምና ክትትል በጊዜ ካልተጀመረ ከ5 እስከ 10 ዓምታት ዉሰጥ ባለ ጊዜ ኤድስ ሊከሰት ይችላል።
 • በኤቸ አይቪ መያዛቸውን እንዳወቁ የሕክምና ክትትል የጀመሩ ሰዎች ጤናማ ሕይወትን መምራት ይችላሉ

 

ኤች አይቪ እንዴት ይሰራጫል ?

ኤች አይቪ የሚስፋፋዉ ከታች በተዘረዘሩ በቫይረሱ በትበከሉ የሰዉነት ፈሳሾች ነዉ፣

 • ደም
 • ዘር ተሸካሚ ፈሳሽ
 • የፊንጢጣ ፈሳሽ
 • የጡት ወተት

ኤች አይቪ ሊስፋፋ የሚቸልበት ብቸኛ መንገድ ያንድ ስዉ የተበከለ ፈሳሽ በሌላዉ ደም ሥር ዉሰጥ በሚከተሉት መንገዶች ሲገባ ነዉ፡

 • በተሰነጠቀ ቆዳ
 • በፊንጢጣ
 • በወንድ ብልት ላይ ያለ ቆዳ እና
 • በወንድ ብልት ቀዳዳ

ኤች አይቪ ሊተላልፍ የማይችልባቸው መንገዶች የሚከተሉት ናቸዉ፤

 • በጤናማና ባልተሰነጠቀ ቆዳ
 • በመተቃቀፍ
 • በመሳሳም
 • በመጨባበጥ
 • ምግብ በጋራ በመብላት
 • በትንኝ ንክሻ እና
 • በሸንት ቤት መቀመጫ

ኤች አይቪ ከናት ወደ ልጅ በሚከተሉት መንገዶች ሊተላለፍ ይችላል፤

 • እርግዝና
 • በወሊድ ወቅት እና
 • ጡት በማጥባት

ካንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው ኤች አይቪ ብቻ እነጂ ኤድስ ሊተላለፉ አይችልም። አንድ ሰው በኤች አይቪና በኤድስ የተያዘ ቢሆንም ሊያሰተላልፉ የሚችለው ኤች አይቪን ብቻ ነዉ።

 

ኤች አይቪ እና ኤድስ ምን ምልክት ያሳያሉ?

ምንም እንኳን ኤድስ አንድ ሰው በኤች አይቪ ከተያዘ በሗላ የሚከሰት ቢሆንም የሁለቱ ምልክቶች የተለያዩ ናቸዉ።

 

ኤች አይቪ

ኤች አይቪ በደም ውስጥ ከገባ ከ2 እስከ 4 ሳምንት በሗላ የሚከተሉት ጉንፋን መሰል ምልክቶች ሊያስከትል ይችላል።

 • ትኩሳት
 • የጉሮሮ ሕመም
 • እራስ ሕመም
 • የጡንቻ ሕመም
 • ያጥንት መገጣጠሚያ ሕመም እና
 • የእጢ እብጠት

የኤች አይቪ ምልክቶች በራሳቸዉ ይጠፋሉ። ከ5 እስከ 10 ዓምታትም ከላይ ከተጠቀሱት የተለዩ ምልክቶች ላይታዩ ስለሚችሉ አንድ አንድ ሰዎች በኤች አይቪ መያዛቸውን ላይረዱ ይችላሉ።

 

ኤድስ

በደም ውስጥ ያለ ኤች አይቪ ቫይርስ የሕክምና ክትትል ካልተደረገለት ኤድስ ሊከሰት ይችላል። ኤድስን ለመከላከል ለሕክምና እርዳታ ቅደሚያ መስጠት ከሞላ ጎደል ጤናማ ኑሮን ለመኖር ያስችላል።

ኤድስ የሚያሳየዉ ምልክቶቸ እነደሚከተሉት ናቸዉ፡

 • የሳምባ ምች
 • በቆዳ ላይ የነቀርሳ እባጮች
 • የቆዳ በሽታ
 • ነረቭ የሚያጠቃ የቆዳ ሽፍታ ሕመም ( shingles)
 • ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ተቅማጥ
 • ምክንያቱን ለማስረዳት የሚያዳግት ክብደት መቀነስ

 

ሕመሙ ቢሰማዎት ምን ማድረግ ይኖርብዎታል ?

የኤች አይቪና የኤድስ ምልክቶች እየታዩብኝ ነዉ ብለዉ ካመኑ የሕክምና ባለሞያ በማየት

 • የደም ምርመራ ያድርጉ
 • በምክር ይረዱ
 • ሕከምና ይከታተሉ

በቫይረሱ ከተያዙ እንደሚከተሉት ያሉ ሰዎችን ማሳወቅ የስፈልጋል፡

 • ለቀደሞና ለወቅታዊ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አጋሮችዎ እና
 • ያደንዛዠ እፅ መዉስጂያ መሳሪያዎችን ሲጋርዋቸው የነበሩ ሰዎች

 

ለግበረ ሥጋ ግንኙነት አጋር(ሮች) ማሳወቅ

ለግብር ሥጋ አጋርዎ(ሮች) በኤች አይቪ እነደተያዙ መናገሩ የሚከብድዎት ከሆነ የጤና ሕክምና ሰጪዉን እርዳታ ይጠይቁ::

ባካናዳ ህግ ለግብር ሥጋ አጋርዎ በኤች አይቪ እነደተያዙ መናገር ግዴታ ሊኖርብዎት ይችላል።

 

ኤች አይቪን አንዴት መከላከል ይቻላል?

ኤች አይቪ መድሃኒት የለውም። ኤች አይቪ በደምዎ ካለ የእድሜ ማራዘሚያ መድሃኒት ክትትል ማድረግ ይችላሉ።

የእድሜ ማራዘሚያ መድሃኒትዎች በሚከተሉት መንገዶች ይረዳሉ፥

 • የቫይረሱን መጠን ከደም ውስጥ በመቀነስ
 • በሰውነት ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት በመቀነስ እና
 • የሰውነትን የበሸታ የመከላከል ሃይል በመጨመር ሌሎች በሸታዎችን ይከላከላል

 

ህክምናውም…….

 • ረጅም አና ጤናማ ህይወት እንዲኖረን ይረዳል
 • ቫይረሱ ወደ ሌሎች የመተላለፍ እድሉን ይቀንሳል

የህክምና ክትትሉን በጊዜ መጀመር ቫየረሱ በደም ውስጥ አንድሌለ ያህል ጤናማ ኑሮን ለመኖር ይረዳል። ከቫይርሱ ጋር ተያይዘው ለሚመጡ የጤና እክሎችም የተለያዩ የህክምና እርዳታዎች ይገኛሉ

 

በካናዳ ውስጥ ምን ያህል ሰው ከኤች አይቪ ቫይረስ ጋር ይኖራል

በ 2014 ማብቂያ ላይ በተደርገው ግምት በካናዳ ውስጥ ከ 54,000 – 76,000 የሚያህሉ ስዎች ከቫይረሱ ጋር ይኖራሉ።

በካናዳ ውስጥ በግምት 5 በቫይረሱ ከተያዙ ስዎች ውስጥ አንዱ/ዋ የኤች አይቪ ምርመራ አድርጎ/ጋ ቫይርሱ በደሙ/ዋ እንዳለ አያውቅም/አታውቅም